Skip to main content

ለስራ ዝግጁነት ለተማሪዎች

አማራጮችን አስሱ


ለMCPS ፕሮግራሞች አቀባበል

በት/ቤታችሁ በርካታ ልዩ ፕሮግራሞች አብዛኛውን ጊዜ ይገኛሉ። ወይም በአካባቢ ወይም በካውንቲ-አቀፍ ፕሮግራም ለመሳተፍ መምረጥ ትችላላችሁ። የማመልከቻና የመቀበያ ሂደቶች እንደየፕሮግራሙ ይለያያሉ። የመረጣችሁት ፕሮግራም የአካባቢ ወይም የማመልከቻ አስፈላጊነት እንዳለው ለመወሰን ከዚህ በታች ያሉትን ፈርጆች ተመልከቱ።

ማመልከቻ

ፉክክር ያለውና የተወሰኑ የመቀመጫ ቁጥሮች ያሉት ፕሮግራም ተማሪዎች ማመልከቻ እንዲሞሉና የተወሰኑ የመግቢያ መስፈርቶች እንዲያሟሉ የሚጠይቅ ፕሮግራም። ይህ የፅሁፍ ማመልከቻን ወይም አንድ ፖርትፎልዮ/የማስረጃዎች ሰነድን ገቢ ማድረግን ሊያካትት ይችላል። የተወሰኑ ፕሮግራሞች ማመልከቻዎች ከካውንቲ አቀፍ ይቀበላሉ፣ ሌሎች ደሞ ማመልከቻዎች ከተወሰኑ የካውንቲ አካባቢዎች ይቀበላሉ።

Choice/ኮንሶርሻ

ተማሪዎች፣ እያንዳንዳቸው ከተወሰነ ጭብጥ ወይም የስራ መስክ ጋር የተዛመዱ የተለዩ ኮርሶች ከሚያቀርቡ በአንድ በተወሰነ ገጸምድራዊ ክልል ካሉ በርካታ ት/ቤቶች፣ አንዱን መምረጥ ይችላሉ። ተማሪዎች የሚፈልጉትን ት/ቤት የሚለይ ፎርም ገቢ ማድረግ አለባቸው። ምንም እንኳን ብዙዎቹ የመጀመርያ ምርጫቸውን የሚያገኙ ቢሆንም፣ ዋስትና የለውም።

Middle School Magnet Consortium/የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ማግኔት ኮንሶርሻ (MSMC) ከካውንቲው ከዳር እስከዳር ከሚገኙ ተማሪዎች የሚቀርቡ የchoice ማመልከቻዎችን ይቀበላል። በMSMC ክልል መስክ ውስጥ የሚኖሩ ተማሪዎች ከሶስቱ የማግኔት የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች አንዱ ጋ የመቀመጫ ዋስትና አላቸው።

የአካባቢ

እያንዳንዱ የMCPS ት/ቤት የሁሉንም ተማሪዎች ፍላጎቶች የሚፈታትገንና የሚያሟላ አጠቃላይ የትምህርት ፕሮግራም ያቀርባል። የተወሰኑ ት/ቤቶች ት/ቤቱን ለሚከታተሉ ተማሪዎች ልዮ ፕሮግራሞችንም ያቀርባሉ። "የአካባቢ ት/ቤት" ፕሮግራሞች ይባላሉ እናም በአካባቢው ት/ቤት ለተመደቡ ተማሪዎች ብቻ ይገኛሉ።

ለዝርዝሮች የአካባቢ ት/ቤታችሁን ተገናኙ ወይም የናንተን የት/ቤት ድርጣብያ ይፈትሹ።

ክልል

በተወሰነ የካውንቲው ጂዮግራፊካዊ ክልል ለሚኖሩ ተማሪዎች በማመልከቻ የሚገኝ። ለዝርዝሮች ት/ቤድቶችን በተናጠል ተገናኙ።

የዝፍቀት/Immersion ሎተሪ

ወደ ውጭ ቋንቋ ዝፍቀት/immersion ፕሮግራም የመግባት ጥያቄዎች ለሙአለህፃናት ወይም ለ1ኛ ክፍል ተማሪዎች ካለው ፕሮግራም አቅም በላይ ከሆኑ ሎተሪ ሊካሄድ ይችላል። ለሌሎች ክፍሎች መግቢያ የሚወሰነው በቋንቋ ችሎታና በክፍት ቦታ መጠን ነው። ስለ ዝፍቀት ፕሮግራማ(ሞቻ)ቸው ት/ቤቶችን በተናጠል ተገናኙ።

ስለ ልዩ ፕሮግራሞች ተጨማሪ መረጃዎች፣ አማራጮች Adobe PDF icon square፣ የካውንቲ አቀፍ ፕሮግራሞች መመርያን፣ አውርዱ።


ኤለሜንታሪ ት/ቤት

መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

^ Back to Top