Is this email not displaying correctly? View it in your browser. Date: May 10, 2016

መልእክት ከInterim Superintendent Larry A. Bowers

በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ኮርሶች የሰሜስተር ማርኮች ስሌት ለውጦች የሚጀምሩት በሚመጣው የትምህርት አመት ነው

የተከበራችሁ የመካከለኛና የሁለተኛ ደረጃ ወላጆች/አሳዳጊዎችና ተማሪዎች፡-

ባለፈው ፎል፣ የትምህርት ቦርድ ባለሁለት-ሰአት የሴመስተር የመጨረሻ ፈተናዎችን ሰርዞ፣ ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ፣ በተወሰኑ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ በሩብ-አመት የማርክ መስጫ ወቅት/period ግምገማዎች ተካቸው። የትምህርት ቦርድ መመርያ IKA፣ ማርክ አሰጣጥ/Grading እና ዘገባ፣ ለውጥ የተደረገው በመማርያ ክፍል ውስጥ በተማሪዎች ላይ የፈተና ጭነት እንዲቀነስና የጠቃሚ የትምህርት ጊዜን እንዲጨመር ከወላጆች፣ ተማሪዎች፣ እና ከመምህራን ለመነጨው ጠንካራ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት ነው። ከስሜስተር ፈተናዎች ወደ ሩብ-አመት የማርክ መስጫ ወቅት ግምገማዎች ስንሸጋገር፣ ግምገመዎቹ ጠንካራ፣ ከኣዳድስ መመዘኛዎች ጋር የተቀናጁ፣ እና የትምህርት ተቀባይነታቸውን እንዲያሻሽሉ ትርጉም ያዘለ አስተያየት ለተማሪዎች የሚያቀርቡ መሆናቸውን እናረጋግጣለን። ስለ የMontgomery County Public Schools (MCPS) የግምገማ ስልትና ስለትግባሬው ዝርዝር የጊዜ ፕሮግራም በMCPS ድር ጣቢያ በwww.montgomeryschoolsmd.org “assessment strategyን” በመፈለግ ተጨማሪ መረጃዎች ማግኘት ትችላላችሁ።

በሰሜስተር ፈተናዎች በተደረጉ ለውጦችና  በአድሶቹ የሩብ-አመት ግምገማዎች ትግ\ባሬ ውጤቶች ምክንያት፣ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ኮርሶች የሰሜስተር ማርክ አሰላል ዘዴ ላይም ተጨማሪ ለውጦች ይኖራሉ። የMCPS ሰራተኞች ከት/ቤትና ከማህበረሰብ ባለጉዳዮች፣ ኮሌጆችንና ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ፣ ሰፊ አስተያየት ሰብስበው፣ የተለያዩ የት/ቤት ዲስትሪክቶች ማርኮች ለወደፊት እንደሚሰሉ አወሳሰን የማርክ አሰጣት ልምዶችን አገናዘቡ።  MCPS፣ ከ2016–2017 የትምህርት አመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን፣ በፊደል ማርክ አሰጣጥ ስርአት መገልገሉን በመቀጠል የሰሜስተርን ማርክ እንደሚከተለው ያሰላል፡-

የማርክ መስጫ ወቅት ግምገማዎች

  • በተወሰኑ ኮርሶች፣ በየሩብ-አመት አንድ ጊዜ ሚዛናቸውን የጠበቁ/standardized የማርክ መስጫ ግምገመዎች ተሰጥተው የያንዳንዱ ማርክ መስጫ ወቅት ማርክ አማካይ/weighted 10%ኛው ይሰጣል። ይህ ለማርክ መስጫ ወቅቱ ወደ ፊደል ማርክ ይሰላል። ይህ ተግባራዊ የሚሆነው በካውንቲ-አቀፍ ደረጃ በእንግሊዘኛ፣ ሂሳብ፣ ሳይንስ፣ ማህበራዊ ጥናቶች፣ የአለም ቋንቋዎች፣ እና በቴክኖሎጂ ቀደም ብለው የመጨረሻ ፈተና ለነበራቸው ኮርሶች ብቻ ነው።
  • በነዚህ ኮርሶች፣ ተማሪዎችና ወላጆች በሴመስተሩ ውስጥ የማርክ መስጫ ወቅት ግምገማዎች ውጤቶችን ይመለከቱ ዘንድ የተለየ የማርክ አሰጣጥ ፈርጅ መስመር ላይ ይታያል። 
  • በባለጉዳዮች ፍላጎትና አስተያየት በመመስረት፣ ግምገማ ከተሰጠ በኋላ ግምገማዎቹን ተማሪዎች ወደ ቤት ይዘው እንዲሄዱ ይፈቀዳል፣ ይህም በአሁኑ የመጨረሻ ፈተናዎች አሰጣጥ ተፈቅዶ አያውቅም። 

የሰሜስተር የማርክ/Grade አሰላል

  • ለወደፊት ልዩው የመጨረሻ ፈተና ማርክ ከተማሪ ሪፖርት ካርድ ይወገዳል።
  • በአሁኑ ወቅት የመጨረሻ ፈተና የሌላቸው ኮርሶች የሴሜስተር ማርክ ስሌቶች ጋር በተመሳሳይ፣ የሴሜስተር ማርክ የሚሰላው በያንዳንዱ የማርክ መስጫ ወቅት የፊደል ውጤቶች በመገልገል ነው።
  • ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ኮርሶች፣ የሰሜስተሩ ማርክ የሚሰላው የያንዳንዱ የማርክ መስጫ ወቅት የፊደል ማርክ አማካይ በማስላት ነው፣ በ“quality point” ግምግማ/ምደባ በመገልገል (A = 4, B =3, C = 2, D = 1, E = 0)።
  • አዲሱ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ኮርሶች የሰሜስተር ማርክ ስሌት በአሁኑ ወቅት በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ኮርሶችና በሰመር ት/ቤት አገልግሎት ላይ ባለው በተመሳሳይ የquality point ስሌት ይጠቀማል።
  • የMCPS የማርክ ስሌት ሰንጠረዦች ከሞላ ጎደል ልዩነት አይኖራቸውም፣ ከዝቅ አድርጎ/downward trend ማርኮችን ከመስጠት አዝማሚያ ይልቅ በአማካዩ ከመተካት በስተቀር። የታደሰው የማርክ አሰጣጥ ሰንጠረዥ ከዚህ ይቀጥላል።

የተከለሰ የማርክ አሰጣጥ ሰንጠረዥ
ፊደሎች የሚያመለክቱት MP1 MP2 = የሰሜስተር ማርክ

AA = A BA = A CA = B DA = B EA = C
AB = A* BB = B CB = B DB = C EB = C
AC = B BC = B* CC = C DC = C EC = D
AD = B* BD = C CD = C* DD = D ED = D
AE = C BE = C* CE = D DE = E EE = E

MP1—የሰሜስተሩ የመጀመርያ ማርክ መስጫ ወቅት ማርክ፤ MP2—የሰሜስተሩ የሁለተኛ ማርክ መስጫ ወቅት ማርክ
በ * እስካልተመለከተ በስተቀር፣ በላይኛው ሰንጠረዥ ውስጥ የሚገኙ ስሌቶች በአሁኑ ወቅት ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ማርክ ማድረጊያ ሰንጠረዥ ጋር ተመሳሳይ ናቸው።

ይህ አዲስ የማርክ መስጫ ስሌት ለግምገማና ለኮሌጅ ተፈላጊ ግምገማዎች በመመዘኛ-የተመሰረተ መዳረሻዎች ጋር ይቀናጃል እናም ርትአዊ፣ ስሙሙ፣ እና ተማሪዎችና ወላጆች በቀላሉ ሊገነዘቡት የሚችሉ የማርክ አሰጣጥ መዋቅር ይሰጣል። የሆኑ ጥያቄዎች ካሏችሁ፣ ስለ የMCPS ማርክ አሰጣጥና የዘገባ መመርያዎች ልዩና የተወሰነ መረጃ አባካችሁ ከልጃችሁ ት/ቤት ጋር ተገናኙ።

Sincerely,

Larry A. Bowers
Interim Superintendent of Schools