MCPS QuickNotes 

ክቡራትና ክቡራን ተመልካቾቻን ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የሚተላለፉ ትምህርት ነክ ዘገባዎችን እንደሚከተለው በአማርኛ ቋንቋ እናስተላልፋለን።

የ 2019 – 2020 የትምህርት ዓመት የሥራ እቅድ ተጀምሯል። የትምህርት ዓመቱ  182 የትምህርት ቀናት፣ የስፕሪንግ እረፍት 10 ቀን እና በየሴሚስተሩ መሃከል አንዳንድ የፕሮፌሽናል ደቨሎፕመንት ቀኖች ይኖሩታል።

የሆነ ሆኖ በገቨርነር ላሪ ሆገን አማካይነት ኦክቶበር 11/2016 የተደነገገው የትምህርት ካላንደር የ2019 -2020 የትምህርት ዓመት እስከሚገባደድ ድረስ በሥራ ላይ ይቆያል።

 

የመጀመሪያው የተማሪዎች ሪፖርት ካርድ ማክሰኞ ኖቬምበር 20 ወደቤት ይላካል። እንዲሁም ፌብሩወሪ 6፣ ኤፕሪል 19፣ እና ጁን 27 የተማሪዎች ሪፖርት ካርድ ወደየቤታቸው ይደርሳል። በመካከለኛ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚማሩ ልጆች ያሏቸው ወላጆች ዓመቱን በሙሉ myMCPS parent portal ላይ የልጆቻቸውን የትምህርት ውጤት ለመከታተል የሚችሉ ሲሆን የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ወላጆችም የልጆቻቸውን የትምህርት አቋም እና ሪፖርት ካርዶችን ለመቆጣጠር ይችላሉ።

ምርጥ እና ብሩህ የሆኑ መምህራን፣ የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች፣ እና ርዕሰ መምህራንን ለተለያዩ ሽልማቶች የመጠቆሚያው ጊዜ አሁን ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በአገልግሎቶቻቸው ልቀው ለሚገኙ እና ልዩ አስተዋጽኦ  ላበረከቱ ሽልማቶችን ለመስጠት በርካታ መሰናዶችዎች ተዘጋጅተዋ፤። ለተለያዩ አይነት ሽልማቶች የመጠቆሚያው የጊዜ ገደብ ከጃኑዋሪ 4 እስከ 11 ስለሚጠናቀቅ አሁኑኑ እንድትጠቁሙ በአክብሮት እንጠይቃለን

 ከባድ/መጥፎ የአየር ሁኔታ ሲከሰት ስለት/ቤት መዘጋት፣ ዘግይቶ እንደሚከፈት እና በቅድሚያ እንደሚሰናበቱ ለወላጆች መልእክት ለማስተላለፍ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በርካታ ስልቶችን ይጠቀማል። እነዚህም AlertMCPS፣ የ MCPS ድረ-ገፅ፣ Comcast 34 Verizon 36 ወይም RCN 89 የተሰኙ የ MCPS ኬብል ቻነሎች እና በስልክ ሪኮርድ የተደረጉ መልእክቶች፣ እንዲሁም Ask MCPS የተሰኘ የስልክ መስመር ናቸው። እንዲሁም በትዊተርና በአካባቢ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች መልእክቶች ይተላለፋሉ። ስለዚህ ለድንገተኛ/ለአስቸኳይ ጊዜ ወቅታዊ ኢንፎርሜሽን በልጆቻቸው ፋይል ላይ  መኖሩን ወላጆች እንዲያረጋግጡ በአክብሮት እናሳስባለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የወደፊት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራሞችን ለመገንባት በዋና የአካደሚክ ኃላፊ አማካይነት ማህበረሰብን የሚያሳትፉ ሦስት ውይይቶች ይካሄዳሉ። ውይይቶቹ የሚያተኩሩት የ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለወደፊት ወደ ኮሌጅ መግቢያ እና ለሥራ ዝግጁነት የሚያግዙ ምን ዓይነት ፕሮግራሞች መሰጠት እንዳለባቸው ከህብረተሰቡ ጋር ለመመካከር ስለሆነ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ የሥራ ባልደረቦች፣ እና የማህበረሰብ አባላት እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።