Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: January 11, 2019

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ(MCPS) ማህበረሰብ
 
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ጃኑዋሪ 8 በተካሄደው የስራ ስብሰባ ሁለት ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል፦ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በቅርቡ የተደረገውን የፖሊሲ ክለሳ "Policy FAA" አስመልክቶ የክፍል መጠን እና የወቅቱን የትምህርት ቤት እና የክለስተር ድንበሮችን የትምህርት መገልገያዎች እቅድ/Educational Facilities Planning
 
የክፍል መጠንን መፈተሽ
 
ወላጆች፣ ሠራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የመማሪያ ክፍል መጠን ያደረባቸውን ስጋት ገልጸውልናል። ሚ/ስ ፓትሪሽያ ኦኔል፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የትምህርት ቦርድ ምክትል ፕሪዚዳንት/ Mrs. Patricia O’Neill, MCPS Board of Education Vice President/ የትምህርት ሥርዓታችን አሁን ያለውን የመማሪያ ክፍል መጠን ለመጠቀም ያስፈለገበትን አመጣጥ ምክንያት ታሪካዊ ዳራ ማጥናት፣ የዲስትሪክቱን ወቅታዊ ሁኔታ፣ እና በሥራ ላይ የሚገኘውን የመማሪያ ክፍል መጠን/ብዛት መመሪያ ለመለወጥ የሚያስገድዱ እውነታዎችን በባጀት ግብአት ላይ ከሚኖረው ተጽ እኖ አንፃር  መመርመር አስፈላጊ እንደሆነ  ያቀረቡትን ሃሳብ ቦርዱ በሙሉ ድምፅ ተቀብሎታል።
 
 በ 2008 ከፍተኛ የኤኮኖሚ ቀውስ በኋላ የሪጅን/ክልላዊ መልሶ ለመገንባት በዲስትሪክታችን ያስከተለው የፋይናንስ ቀውስ በሠራተኞች አቀጣጠር/ምደባ እና የትምህርት መርጃ ግብአቶች የተዛነፈውን አሠራር ለማስተካከል/ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት ተከትሎ MCPS በተለይም የመማሪያ ክፍል መጠን በትክክል በተለያየ አቅጣጫ ለማጥናት እና ለመገምገም አይነተኛው ወቅት አሁን ነው።
 
MCPS ተሳትፏል በስቴት የሚደገፍ የስትራቴጂ እቅድ/ፕላን መዘርጋት እና የትምህርት መርጃ መገልገያዎች ምደባ ግብረኃይል ማህበረሰብእና  በቦርድ-የሚደገፍ የትምህርት ግብአት ስትራተጂ አጋርነትን (ERS) ሥራ እንደቀጠለ ነው ። ይህ ሥራ በትምህርት ቤቶቻችን የትምህርት ግብአቶች እንዴት በጥቅም ላይ እንደሚውሉ፣ በት/ቤቶቻችን እና በዲስትሪክቱ በጠቅላላ የተማሪዎችን እና የሠራተኞችን ፍላጎት ለማሟላት ተማሪዎች እና ሠራተኞች እንዴት እንደሚመደቡና የክፍል መጠን/ብዛትን ለማወቅ ይረዳል። ERS ግኝቶቹን ጁን ላይ ለቦርድ ያቀርባል። በተጨማሪ፦ ለአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የመማሪያ ክፍል መጠን/ስፋት/ብዛት ዳሽ ቦርድ እንደ .. አካል በቅርብ ጊዜ ገቢራዊ ይደረጋል MCPS Data Dashboardበ MCPS Data Dashboard ላይ ይመልከቱ፦ የትምህርት ቤቶች ዋና የበላይ ተቆጣጣሪ/ሱፐርኢንተንዳንት የመማሪያ ክፍልን መጠን/ስፋት ለማሻሻል ከማህበረሰቡ ከሚገኙት ግብአቶች ጋር እነዚን ግኝቶች ያመዛዝናል።
 
ለበርካታ ዓመታት የክፍል መጠን/ብዛት የመነጋገሪያ ርእስ እንደነበረ ስለምናውቅ በወቅቱ ያለውን መመሪያ በዝርዝር ለማየት እና ለወደፊት ውሳኔ አሰጣጥ እንዲያመች ሁለንተናዊ ጥናት በማድረግ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኞች ነን።
 
በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች፦ የክፍል መጠን/ስፋት/ብዛትን ማጥናት
 
የወሰን/ድንበር ዝርዝር ጥናት
 
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ MCPS የሚመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር በሚያስገርም ሁኔታ ጨምሯል፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ እድገት እና የቤቶች ፍላጎት እየቀጠለ ይሄዳል።  ሚ/ስ አናንያ ታዲኮንዳ፣ ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል/Ms. Ananya Tadikonda, the Student Member of the Board of Education/ አሁን ያለው የትምህርት ፋሲሊቲ እና የክለስተር ድንበሮች ምን ያክል አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ጠቀሜታ እንዳላቸው በጥልቀት እንዲገመገም የውሳኔ ሃሳብ አቅርባለች።
 
ይህ ግምገማ ንብረቶቻችንን፣ ፍትኃዊ የትምህርት አካባቢዎችን፣ የተማሪዎቻችንን ብዝሃነት ጨምሮ በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀም እንደሚያስችለን ፖሊሲ/policyእሴቶቻችንን በሚያንጸባርቅ መልኩ ለመጠቀም እንድንችል ይረዳናል።
 
ቦርዱ ካውንቲ አቀፍ የምልከታ መረጃዎችን በማግኘት እነዚህን ትንተናዎች ከአማካሪ ባለሙያ ጋር በዝርዝር ያጠናል። ማናቸውም የወደፊት ሂደቶች አራቱን ዋና መልህቆችን ስብጥር፣ ማህበረሰቡ ለት/ቤት ያለው ቅርበት ወይም ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ በየጊዜው የሚከናወኑ ተግባሮች ምደባ-ለምሳሌ ትምህርት ቤቶችን የመከለል/ወሰን ተደጋጋሚነት፣ ወይም የትምህርት ቤት ምደባ፣ እና ትምህርት ቤቶችን በአግባቡ በመጠቀም ሁኔታዎችን ያገናዘበ ይሆናል።
 
በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች፡ የወሰን ትንታኔ
 
እነዚህ ሁለት ጥረቶች በየትኛውም ደረጃ የማህበረሰቡን ተሳትፎ ያሚያማክሉ ይሆናል። በዚህ ግምገማ ቅርጽ እና ትኩረት ላይ ግብአቶችን እና አስተያየቶችን ለማሰባሰብ በመጪዎቹ ወራት ወደ ባለድርሻ አካላት እንደርሳለን። ሥራው በተቀላጠፈ መጠን ከእርስዎ ጋር የሚኖረን የተሳትፎ ግንኙነት ይቀጥላል። ጥናቱ ከሴፕቴምበር 30/2019 ወዲህ ያለውን የተማሪዎች ምዝገባ መረጃ ይጠቀማል፣ እና ስፕሪንግ 2020 ላይ ለቦርድ ይቀርባል።
 
ተማሪዎቻችንን በከፍተኛ ጥራት ለማገልገል ያለንን የትምህርት መርጃዎችን እና መገልገያዎቻችንን በጥራት እና በቅልጥፍና መጠቀም እንዳለብን ለማህበረሰባችን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለብን። እነዚህ ጉዳዮች ለእርስዎ በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን ስለምናውቅ በጥልቀት ለመመርመር/ለመፈተሽ ቁርጠኞች ነው።
 
ሁለቱም ጥናቶች ከተደረጉ በኋላ፣ ቦርዱ ግብረመልሶችን፣ ግምት ውስጥ በማስገባት መወሰድ ያለባቸው አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎች ካሉ፣ ግልጽነት ባለው የአሠራር ሂደት መረጃዎችን በትንታኔ/በዝርዝር ይመለከታቸዋል። ለማናቸውንም ውሳኔዎቻችን፣ መረጃ፣ እና ከእርስዎ በምናገኘው ግብረመልስ ላይ ተመርኩዘን ማህበረሰባችንን በማሳተፍ እንቀጥላለን።
 
ከእርስዎ ጋር በጋራ ለመሥራት ተስፋ እናደርጋለን
 
ከሰላምታ ጋር
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ