English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어 | አማርኛ | Portuguese
በማስተማር፣ በአመራር፣ እና በመማር ረገድ ዘር፣ ጎሣ፣ እና ባህል ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። ለበርካታ ዓመታት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለተማሪዎች ጥብቅ፣ ትርጉም ያለው ትምህርት ለመስጠት ሲሠራ የቆየ ነው፣ ነገር ግን ሁሉ ተማሪዎች ከፍተኛ ደረጃዎች ላይ እየደረሱ አለመሆኑን መረጃዎች ያረጋግጣሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በግልጽነት እና በድፍረት የሚጠይቀው፣ ህዝባዊ ትምህርት ሁሉንም ተማሪዎች በእኩልነት እና በፍትሃዊነት ማገልገል እንደሚገባ የሚያምን ሲሆን ይህም የፍትሃዊነትና የሚዛናዊነት ጉዞ እምነቱ ለዲስትሪክት አቀፍ እሴቶች፣ ለስትራቴጂያዊ እቅድ እና የበጀት ዝግጅት ማዕከል ነው። የዛሬው "ሁሉም ነገር፦ የእኩልነትና ውጤታማነት ማዕቀፍ" የሚያርፈው ለዓመታት በእውቀት ላይ በተመሰረተ፣ ጠንክሮ በመስራት መሠረት ላይ ነው ። የዚህ ስራ አስፈላጊ ማጣቀሻዎች-ማመሣከሪያዎች በዚህ ድረገጽ ላይ ቀርበዋል።
የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተልእኮ ሁሉም ተማሪ በኮሌጅ ፣ በሥራ፣ እና በማህበረሰቡ ዘንድ በወገንተኝነት ያልሆነ ስኬታማ ለመሆን የሚያስችሉት/የሚያስችላት የአካደሚክ፣ ፕሮብሌሞችን/ችግሮችን የመፍታት የፈጠራ ችሎታ፣ እና ማህበራዊ እና ስሜታዊ ክህሎቶች እንዲኖሩት/እንዲኖሯት ማረጋገጥ ነው። በርካታ ተማሪዎቻችን በከፍተኛ ደረጃ ስኬታማነትን እየተጎናጸፉ ቢሆንም፣ ብዙዎች ግን ይሄን አድልና ድጋፍ እንዲሁም ያላቸውን እምቅ አቅም በቁምነገር ለመጠቀም የሚያስችላቸው መገልገያ ግብአቶችን አግኝተው አያገኙም፣ በሁሉም የመማሪያ ክፍሎች ፣ እና በሁሉም ት/ቤቶቻችን፣ ለሁሉም ተማሪዎች በእድል እና በስኬት ረገድ ያለውን ክፍተቶች በመዝጋት በተማሪ ውጤቶች ላይ ያለዉን ልዩነቶች/የአለመመጣጠን ለመፍታት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በቁርጠኝነት ይሰራል። (በሁሉም ቋንቋዎች ይገኛል።)
1
የተማሪን መማር በመማሪያ ክፍል ዉስጥ፣ በዲስትሪክት እና በውጭ ፈርጆች/ዘርፎች የሚገመግሙ/የሚዳስሱ በርካታ እርምጃዎች
2
በርካታ መመዘኛ መስፈርቶችን የማያሟሉ ተማሪዎችን ለመለየት መረጃ/ዳታ የመጠቀም ስልት እና ያሟሉትን ደግሞ ቀጣይነት እንደሚኖራቸው ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው የማሻሻያ ናሙና/ሞዴል
3
በርካታ መመዘኛ መስፈርቶችን የማያሟሉ ተማሪዎችን ለመለየት መረጃ/ዳታ የመጠቀም ስልት እና ያሟሉትን ደግሞ ቀጣይነት እንደሚኖራቸው ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው የማሻሻያ ናሙና/ሞዴል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የፍትሃዊነትና የሚዛናዊነት ሃላፊነትና ተጠያቂነት ሞዴል* ስለትምህርት ቤቶች ስኬታማነት ዝርዝር ዳሰሳ የሚያደርግ ሲሆን የሁሉንም ተማሪዎች ክንውን በይፋ ሪፖርት ይሰጣል። የ ተገቢነት፣ ትክክለኛነት፣ ሚዛናዊነት-ተጠያቂነት/ሀላፊነት አርአያ አይነት ከተለመደው አይነት የስቴት እና የፌደራል ጅምላ የሪፖርት አቀራረብ ባለፈ መልኩ/ባሻገር ተመሣሣይ/እኩል ተደራሽ እድል ወይም እንደሌሎች ስኬታማ የመሆን እድል ባላገኙት የተማሪዎች ትኩረት ቡድን ላይ በዝርዝር ሪፖርት የማድረግ ሥራ ይሠራል።
እንዴት እናውቃለን? ካልሆነስ፣ ለምን አልሆነም?
ትምህርት ቤቶች ሠራተኞችን፣ ጊዜን እና ገንዘብን በተማሪ ውጤታማነት የስኬት ማእቀፍ ሚዛን ሲታይ በአምስቱ የትኩረት ቡድኖች ክንዋኔ አንፃር ፍትሃዊ የሪሶርሶች ተደራሽነትን (EAR) ሲስተሙ እንዴት በትክክለኛ ሚዛናዊነት እየተጠቀመ እንደሆነ በከፊል ይመረምራል። በሲስተሙ የሚገኙ ሪሶርሶች ምደባ እና አጠቃቀምን በጥልቀት ግምገማ የማድረግ ዋናው ግብ አስቀድሞውኑ የተተለመ በዘር ወይም በገቢ መጠን ላይ የሚመሠረት ሚዛን ያልጠበቀ የተማሪ ስኬታማነትን ለመቀነስ ነው።
ስለዚህ ምን ማድረግ ይኖርብናል?
ሜይ 3/2019 በ 9:00 a.m. EDT
በሞንቶጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ብዙ የካውንቲአችን ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች ከፍተኛ አድናቆት የሚገባቸው እና ሽልማቶችንም ያገኙ ቢሆንም ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ግን በአንፃሩ የስኬት ልዩነት ክፍተቱ እያደገ ሄዷል። የካውንቲው መሪዎች ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ክፍተቱ ተባብሶ ቀጥሎአል፣ በተወዛጋቢ መረጃ ተዳፍኖ አንዳንድ ተማሪዎች በትልቅነቱ አንደኛ በሆነው የአገሪቱ የትምህርት ቤት ዲስትሪክት ውስጥ በእኩዮቻቸው ውጤት ሳቢያ እንዲደበዝዙ አስችሏል
ህትመት፦ 2020-07-11 00:49
አብዛኛዎቹን አመታት፥ የጁላይ አራትን በዓል ከቤተሰቤና ከጓደኞቼ ጋር በማሳልፍበት ጊዜ፣ ርችት በሚታይበት ወቅት በልጄ ልጅ ፊት ላይ የሚታየውን ደስታ በመመልከትና ባሳለፍኳቸው ጁላይ 4 ክብረበዓላት የት እንዳለሁ በማሰላሰል በርካታ በዓላትን አልፌአለሁ።
ሜይ 31/2020
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ፈተናዎችን እየተጋፈጥን ስንሄድ፣ እንዴት ሁላችን በአንድነት እንደምንሆን "በዚህ ሁላችን አብረን ነን-all in this together" በሚል ርዕስ ለብዙ ሳምንታት እየጻፍኩ ነበር። ይሁን እንጂ አሁን መግለጽ ያለብኝ መፍትሔ ማግኘት ያለበት ሌላም ችግር በአገራችን አለ። ይኼውም ሁላችንም የሚያጋጥመን የፍትሕና የእኩልነት ችግር ነው፤ ሁላችንም አንድ ላይ ሆነን ሳለ፣ ይህን ቀውስ ግን ሁላችን በአንድ መልክ እያጋጠመን አይደለም - ሌላው ቀርቶ ተቀራራቢነት እንኳ የለውም።
ጃኑወሪ 20/2021
ማንም ሰው በቆዳው ቀለም ወይም በማንነቱ ወይም በሃይማኖቱ ምክንያት ሌላውን ሰው ጠልቶ አይወለድም። ሰዎች ጥላቻን ይማራሉ፤ ጥላቻን መማር ከቻሉ ደግሞ ፍቅርንም መማር ይችላሉ፤ ምክንያቱም ፍቅር ከተቃራኒው (ከጥላቻ) ይልቅ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ በሰዎች ልብ ውስጥ ይሰፋል። - Nelson Mandela/ኔልሰን ማንዴላ
ተማሪዎች ከፍ ያለ የትምህርት ደረጃ ላይ ለመድረስ የደስታ ስሜት ሊሰማቸው ያስፈልጋል። አካላዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋቸዋል። ማንነታቸው የሚከበርላቸው ምህዳር ያስፈልጋቸዋል ከጥላቻና ከአድልዎ ነፃ የሆኑ ትምህርት ቤቶችና ማኅበረሰብ ይፈልጋሉ።
ስለሚዛናዊነትና ፍትሃዊነት ገጽታ በአብዛኛው የሱፐርኢንተንደንቱ ጦማር ላይ ሲገለጽ ቆይቷል፦
ዲሴምበር 19/2019
አብዛኛውን ጊዜ ስናገር የነበረው ስለ እያንዳንዱ ተማሪ ለኮሌጅ ወይም ለሙያ የሚያዘጋጅ ትምህርት እንደሚያገኝ-እንደምታገኝ ለማረጋገጥ ስላለብን የሞራል ግዴታን በሚመለከት ነበር።
ዲሴምበር 4/2019
ፎል መገባደጃ ለእኛ የትምህርት ቤት ሲስተም የባጀት ወቅት ነው። ስለ ባጀት ላይ ላዩን ሲታሰብ፥ ደረቅና አሰልቺ ቢመስልም ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ነገሮች እንድንገመግምና ገንዘባችንን ትኩረት መስጠት ባለብን ነገር ላይ እንድናስቀምጥ ያስችለናል።
ሜይ 30/2020
ልጆች እና ማህበረሰቡ በቅርቡ ስለተከሰተው የጆርጅ ፍሎይድ (George Floyd) እና በረና ቴይለር (Breonna Taylor) አሰቃቂ ግድያ ሲያነቡ፣ ሲያዳምጡ እና ሲመለከቱ በይፋ አውጥተን መናገር የእኛ አጣዳፊና አስቸኳይ የሞራል ግዴታ ይሆናል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ በሚናፖሊስ (Minneapolis) የተፈጸመውን የሚ/ር ፍሎይድ (Mr. Floyd) አሰቃቂ ግድያ እና በሉይስቪል (Louisville) የሚ/ስ ቴይለርን አስከፊ ግድያ ያወግዛል። በተለይ በእነርሱ ላይ ዘግናኝ ግድያ የተፈጸመው በህግ አስከባሪ አማካይነት መሆኑ ተቀባይነት የሌለው ነው። እነዚህ ድርጊቶች ሕዝባችን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ባሠቃዩት የረዥም ጊዜ ታሪካዊ ኢፍትሐዊ ድርጊቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው።
ፕሮጀክቱ ገና ሲጀመር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) በስድስት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ኦዲት የሚያደርግ የውጭ ተቋራጭ እንዲሳተፍ ያደርጋል፦
ዘርና ባሕል በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ፖሊሲዎች፣ ልማዶችና መስተጋብሮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ከመሆናቸውም በላይ በዘር መድልዎ ላይ የተመሠረተ የስኬታማነት እና የውጤት ትንበያን ሊያስከትል ይችላል።
የጥናት ክበቦች ፕሮግራም፣ ቡድኖች ተፈታታኝ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ለማድረግ የሚያስችሏቸውን ግንኙነቶች፣ ግንዛቤዎችና ችሎታዎች እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል።
የውይይቱ ሂደት ተሳታፊዎቹ የሚከተሉትን ነጥቦች እንዲያስተውሉ ይረዳቸዋል፦
ፍትሃዊ ተሃድሶ ማለት ማህበረሰብን፣ ራስን መንከባከብን፣ እና የግጭት አፈታትን የመገንባት አቀራረብ ነው። ይኼውም ለተማሪዎች የሚጠቅም የማህበራዊ ፍትህ መድረክ ነው፦