Amharic 11-09-2023
ኖቬምበር 1, 2023
ስለ አእምሮ ጤንነት ግንዛቤ በዚህ ሳምንት ያክብሩ
MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤት የሳይኮሎጂስቶች ማህበር (MCSPA) ለወጣቶች እና ለቤተሰቦች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከአእምሮ ጤና ባለሙያዎች የመስማት እድል ለመስጠት እስከ ኖቬምበር 4 ድረስ ነፃ ዝግጅቶችን ያስተናግዳሉ። በአካል እና በቨርቹዋል የሚካሄደው የዝግጅቶች ሳምንት፣ ተናጋሪዎችን እና አውደጥናቶችን/ወርክሾፖችን ያካትታል።
ኖቬምበር 1፣ከ6-8 p.m. በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የቀድሞ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋች እና በአሁኑ ጊዜ የዓዕምሮ ጤና ባለሙያ እና አቀንቃኝ የሆኑት ዶ/ር ጄይ ባርኔት ለተማሪዎች ስለ ዓዕምሮ ጤና አስፈላጊነት (ጠቀሜታ)፣ መገለልን ሰለማስወገድ እና እርዳታ ስለመፈለግ (ስለመሻት) ተማሪዎች ለተሳትፏቸው SSL ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። ይህ ዝግጅት MCPS-TV እና MCPS en Español ዩቲዩብ ቻናሎች ላይም በቀጥታ ይተላለፋል። በአካል ለመገኘት ካሰቡ፣ እባክዎን ይመዝገቡ/RSVP።
ሳምንቱ በቨርቹዋል የሪሶርስ አውደ ርዕይ እና በባለሙያዎች የፓነል ውይይት ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 4 ከ11:30 a.m.–1 p.m. ይካሄዳል። በዚህ ዝግጅት ስለ MCPS የአእምሮ ጤና መገልገያዎች/ሪሶርሶች፣ ስለ አገልግሎት ሰጪዎች እና የማህበረሰብ አጋሮች ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው መረጃ ይሰጣል።
ሳምንቱ፦ ጤናማ ልማዶች፣ አወንታዊ የትምህርት አውድን በእኩልነት እና በብዝሃነት መደገፍ፣ እና ማህበራዊ-ስሜታዊ ቃላትን በአግባቡ በመጠቀም ችግሮችን መደገፍን በመሳሰሉ ርእሶች ላይ የተቀረጹ ቪዲዮዎችንም ያካትታል። የአእምሮ ነርቭ ልዩነት/neurodiversity፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ደህንነት፣ ዮጋ እና ህመም ማስታገሻ፣ እና የአደንዛዥ እጽ አጠቃቀም መከላከልን በተመለከተ ከባለሙያዎች ጋር ቃለ ምልልስ ይደረጋል።
በመጪዎቹ መድረኮች ስለ ሥራ ማስኬጃ ባጀት ግንዛቤ ያግኙ
ስለ 2024–2025 የስራ ማስኬጃ በጀት ሂደት የበለጠ ለማወቅ MCPS ተከታታይ የውይይት መድረኮችን አያስተናገደ ነው። ከMCPS አመራር ጋር ለመወያየት እና በቡድን የውይይት ክፍለ ጊዜዎች የመሳተፍ እድል ለማግኘት ይቀላቀሉን። እባክዎን ይሳተፉ እንደሆነ እና የስፓኒሽኛ ወይም የአሜሪካ የምልክት ቋንቋ ትርጉም ያስፈልግዎት እንደሆነ ያሳውቁን።
ዝግጅቶች ይካሄዳሉ፡-
- ሐሙስ፣ ኖቬምበር 2, ከ 6:30–8 p.m., ቨርቹዋል መድረክ። ይህ ዝግጅት MCPS ዋናው የበይነመረብ ገጽ ላይ በቀጥታ ይተላለፋል። ይመዝገቡ/RSVP.
- ማክሰኞ፣ ኖቬምበር 14፣ ከ 6፡30-8፣ ቨርቹዋል ይካሄዳል። ይመዝገቡ/RSVP.
በተጨማሪም እሮብ፣ ኖቬምበር 8 በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች ብቻ ክፍት የሆነ መድረክ ነው።
ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች እና ለሜሪላንድ ቨርቹዋል አካዳሚ ማመልከቻ የሚቀርብበት ጊዜ ኖቬምበር 8 ያበቃል።
የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ParentVUE ላይ የሚገኘውን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት "common application" በመጠቀም ለሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። በተጨማሪም፣ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ለሙያ ዝግጁነት ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች የመረጃ ክፍለ ጊዜዎች ይኖራሉ። ሁሉም ቀኖች በልዩ ፕሮግራሞች ድረ-ገጽ ላይ አሉ።
ማመልከቻዎች የሚቀርቡበት የመጨረሻ ቀን እሮብ፣ ኖቬምበር 8 ነው። ፕሮግራሞችን-በጨረፍታ ስለ ብቁነት፣ እና በተደጋጋሚ ስለሚነሱ ጥያቄዎች በዚህ ድረ ገጽ ላይ ይመልከቱ።
2024-2025 የትምህርት ዓመት ለሞንትጎመሪ ቨርቹዋል አካዳሚ (MVA) ማመልከቻ የሚቀርብበት የመጨረሻው ቀን አርብ፣ ኖቬምበር 3, 2023 ነው። የቨርቹዋል አካዳሚ 2023-2024 የትምህርት ዓመት ሴሚስተር 2 የተጠባባቂዎች ዝርዝር ማመልከቻዎች እንዲሁ ኖቬምበር 3. ይጠናቀቃሉ። ከኖቬምበር 3, 2023 በኋላ እስከ ፌብሩዋሪ. 9, 2024 የሚቀርቡ ማመልከቻዎች ወደ 2024-2025 የተጠባባቂዎች ዝርዝር ውስጥ ይገባሉ።
ለበለጠ መረጃ MVA ድረገጽ ይጎብኙ።
ለአመቱ ምርጥ የድጋፍ ኣገልግሎቶች ሰራተኛ እጩዎችን ለማቅረብ ክፍት ነው
የአመቱ ምርጥ የድጋፍ አገልግሎት ሰራተኛ ሽልማት 2024 እጩዎችን ለማቅረብ አሁን ክፍት ነው። በዚህ አመት፣ MCPS እና SEIU Local 500 ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለማህበረሰቡ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ሲያበረክቱ ሙያዊ ብቃት ለሚያሳዩ 24 የድጋፍ አገልግሎቶች ሰራተኞች እውቅና ይሰጣሉ። ተጠቋሚዎች (ዕጩዎች) በቋሚ የሥራ መደብ ውስጥ ንቁ የድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች መሆን አለባቸው፣ እና ከMCPS ጋር ቢያንስ የሶስት ዓመት አገልግሎት ሊኖራቸው ይገባል። የተሞሉ የጥቆማ ሠነዶች በኤሌክትሮኒክስ ለ memberservices@seiu500.org መቅረብ አለባቸው። ለዓመቱ ምርጥ የድጋፍ ሰጪ አገልግሎቶች ሠራተኛ ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ የሚሰጥበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ዲሴምበር 12. እስከ 5 p.m. ነው።
ለሌሎች መምህር እና አስተዳዳሪ ሽልማቶች እጩዎችን ለመጠቆምም ክፍት ነው። ለሚከተሉት ዕውቅናዎች የሚቀርቡ ሰነዶች እስከ አርብ፣ ዲሴምበር 22 እኩለ ሌሊት ድረስ መቅረብ አለባቸው። ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር ይመልከቱ፦
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የአመቱ ምርጥ መምህር ሽልማት
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የዓመቱ ስኬታማ የመሆን ተስፋ ያለው መምህር ሽልማት
የዋሽንግተን ፖስት የአመቱ ምርጥ አስተማሪ ሽልማት
የሸርሊ ጄ. ሎሪ 'ስለማስተማርዎ እናመሰግናለን' ሽልማት
የሱፐርኢንተንደንት አመታዊ የማርክ ማን የልህቀት እና ስምምነት ሽልማት
የ 2023-2024 የቲያትር ፕሮዳክሽን ይመልከቱ!
በመካከለኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የፎል ወቅት የቲያትር ዝግጅቶች መጋረጃ እየተከፈተ ነው። እስከ 2024 መጀመሪያ ድረስ የሚካሄዱትን ምርጥ ትርኢቶች ለማየት አሁኑኑ ያቅዱ።
ከ“Shrek” and “Mamma Mia” እስከ “Radium Girls” and “Lavender”፣ በ 2023 አልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምሩቅ የተዘጋጁ ኦሪጅናል ስራዎች፣ ለሁሉም ሰው የሚሆን ነገር አለ። ይምጡ!
PSA ውድድር፡ ተናገር/ሪ፣ ህይወት አድን/ኚ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የስቴት ጥብቅና ፅህፈት ቤት ስለ ታዳጊ ወጣቶች የኦፒዮይድ አላግባብ መጠቀምን ወይም ከመጠን በላይ መውሰድን እና በታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚታየውን የፈንታኒል አደጋ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታዳጊዎች ኦሪጅናል ቪዲዮ እንዲፈጥሩ የሚጠይቅ የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያ ውድድር እያዘጋጀ ነው። ውድድሩ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ክፍት ሲሆን፣ የሚሳተፉ ተማሪዎች 10 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
ተማሪዎች በውድድሩ ላይ በግላቸው ወይም በቡድን መሳተፍ ይችላሉ፤ ይሁን እንጂ፣ተማሪዎች ከሁለቱ መንገዶች በአንዱ ብቻ መሳተፍ አለባቸው።
ከፍተኛው ሽልማት $1,000፣ ሁለተኛ ደረጃ $750፣ ሶስተኛ የወጣ እና የደጋፊዎች አሸናፊዎች $500 ያገኛሉ። የገንዘብ ሽልማቶቹ እየተበረከቱ ያሉት በማግኖሊያ ፕሉምቢንግ/Magnolia Plumbing ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ህገወጥ ፈንቴኒልን በመውሰድ ህይወታቸውን ያጡ - ሚካኤል ፒሳርራ እና ማቲው ሎዶን የተባሉ የMCPS ተመራቂ የነበሩ ሁለት ወጣቶችን ለመዘከር ነው።
ሰነዶች የሚቀርቡበት የመጨረሻው ቀን አርብ፣ ኖቬምበር 17 ነው።
እዚህ ያስገቡ/Enter here
ጥያቄ ካለዎት እዚህ ኢሜይል ይላኩ።
መኪና ይለግሱ፣ የግብር ቅነሳ ያግኙ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የተማሪዎች ኦቶሞቲቭ ትሬድስ ፋውንዴሽን (ATF) የመኪና ስጦታዎችን (ልገሳዎችን) ይፈልጋል። ልገሳዎቹ ከ400 በላይ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ያገለገሉ መኪናዎችን እንዴት መመርመር፣ መጠገን እና ማደስ እንደሚችሉ እንዲማሩ ይረዳቸዋል። ATF ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ለተማሪዎች የጥገና፣ የእድሳት፣ የሽያጭ እና የግብይት (ማርኬቲንግ) ተግባራዊ ትምህርት በመስጠት የአውቶሞቲቭ ትምህርትን የሚያበረታታ ድርጅት ነው። የአውቶሞቲቭ ፕሮግራም አንድ አካል በመሆኑ፣ ተማሪዎች በትምህርት ዓመቱ በሦስት የሽያጭ ክፍለጊዜዎች መኪናዎቹን ይሸጣሉ።
ATF ዓመቱን በሙሉ ከሰኞ እስከ አርብ በደማስከስ፣ በጌትስበርግ፣ እና በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በቶማስ ኤዲሰን ሁለተኛ ደረጃ የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት ከ 8 a.m.–3 p.m. ባለው ጊዜ ውስጥ ልገሳዎችን ይቀበላል። ስጦታዎቹ (ልገሳዎቹ) ታክስ የሚያስቀንሱ ሊሆኑ ይችላለ።
ለተጨማሪ መረጃ፣ ATF ድረገጽ ይጎብኙ። የመኪና ልገሳ ለማድረግ ቀጠሮ ለማስያዝ ማይክ ስናይደርን በስልክ ቁጥር 240-740-2047 ያነጋግሩ።
C-SPAN የዘጋቢ ቪድኦ ውድድር ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው።
ከ6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በ C-SPAN ዓመታዊ ብሔራዊ የቪድዮ ዘጋቢ/ዶክመንተሪ "StudentCam" ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፣ ይህም ማህበረሰባችን ላይ ተፅእኖ ስለሚያሳድሩ ጉዳዮች በትኩረት እንዲያስቡ ያበረታታቸዋል።
በዚህ አመት ተማሪዎች "ያለፈውን እያጤኑ ወደፊት መመልከት" ከሚለው ከውድድሩ ጭብጥ ጋር የተገናኘ ርዕስ ላይ ከአምሰት እስክ ስድስት ደቂቃ የሚፈጅ የዘጋቢ/ዶክመንተሪ ቪዲዮ እንዲሰሩ እየተጠየቁ ነው። ተማሪዎች ከሚከተሉት ጥያቄዎች ውስጥ መፍትሄ የሚሰጡበትን አንዱን ጥያቄ እንዲመርጡ ይጠየቃሉ፡"
- በሚቀጥሉት 20 ዓመታት፣ በአሜሪካ ውስጥ ማየት የሚፈልጉት በጣም አስፈላጊው ለውጥ ምንድነው? ለእርስዎ አስፈላጊ (ጠቃሚ) የሆነውን አንድ የተወሰነ ጉዳይ እና ወደፊት ሊያዩዋቸው የሚፈልጓቸውን ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው የፖሊሲዎች፣ የህጎች እና የተግባሮች ዝግመተ ለውጥን በዝርዝር ያስቀምጡ።
- ባለፉት 20 ዓመታት፣ በአሜሪካ ውስጥ በጣም አስፈላጊ የነበረው ለውጥ ምንድን ነው? አንድን የተወሰነ ህግ፣ክስተት ወይም ፈጠራን መርምር\ሪ፣ተፅዕኖውን እና ለምን አስፈላጊ ነው ብለህ እንደምታስብ አስረዳ/ብለሽ እንደምታስቢ አስረጂ።
የማስረከቢያ ቀነ-ገደብ አርብ፣ ጃኑወሪ 19, 2024 ነው።
መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦
ሐሙስ፣ ኖቬምበር 1– የማርክ መስጫ 2ኛ ክፍለጊዜ ይጀምራል
ሐሙስ፣ ኖቬምበር 9 – የሪፖርት ካርድ ስርጭት
ሰኞ፣ ኖቬምበር 6 – የትምህርት ቦርድ ስለ ፋሲሊቲዎች እና ወሰኖች የሚሰማበት ችሎት
ማክሰኞ፣ኖቬምበር 7 – የትምህርት ቦርድ ስለ ፋሲሊቲዎች እና ወሰኖች የሚሰማበት ችሎት
ሐሙስ፣ ኖቬምበር 9 – የትምህርት ቦርድ ስብሰባ